Pages

Saturday, October 27, 2018

ቅዱስ እስጢፋኖስ --- St.Estifani

                                           
🌹💚የቅዱስ እስጢፋኖስ ታሪክ ባጭሩ🌹💚

🌿❤️ እስጢፋኖስ የግሪክ ቋንቋ ሲሆን ትርጓሜውም «አክሊል» ማለት ነው።

🌿❤️ ቅዱስ እስጢፋኖስ በግሪክ ሀገር እንደተወለደ የሚነገርለትና ከክርስቶስ እርገት በኋላም አስራ ሁለቱም ሐዋርያት በጋራ ተሰብስበውና ለአገለግሎት ከመረጡዋቸው ሰባት ዲያቆናት አንዱና ዋነኛው ነበር። ሕዝቡን በማዕድ ያገለግሉ ዘንድ ሰባት ዲያቆናት ተመርጠዋል።
🌿❤️ ከእነዚህ መካከል ቅዱስ እስጢፋኖስ አንዱ ሲሆን ለስድስቱ ዲያቆናት ደግሞ አለቃ ሊቀ ዲያቆን ሆኖ ተሹሟል። ቅዱስ እስጢፋኖስ በማዕድ አገልግሎት ሕዝቡን ከማገልገሉ በተጨማሪ ወንጌልን ይሰብክ ነበር ። ተዐምራትን የማድረግ ጸጋም ተሰጥቶት ነበር በዚህም አገልግሎቱ ብዙዎችን ወደ ክርስትና መልሷል።
🌿❤️ በዚህም አይሁድ በቅናት ተነሳስተው
በሐሰት ከሰሱት ከከተማውም ወደ ውጭ አውጥተው ቄዳር በተባለ ቦታ በድንጋይ ወገሩት በሚወግሩትም ጊዜ ሰማያት ተከፍተው ምሥጢረ ሥላሴን እግዚአብሔርን በሦስትነቱ ተመለከተ።
🌿❤️ ኢየሱስ ክርስቶስንም በአብ ቀኝ ተቀምጦ አየ ። ለሚወግሩትም ሰዎች ከአምላኩ እንዲህ በማለት ምሕረትን ለመነ «ጌታ ሆይ ይህንን ኃጢአት አትቁጠርባቸው» በመጨረሻም «ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል»ብሎ ነፍሱን ሰጠ።
🌿❤️ ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት። ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ። እስጢፋኖስም። ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር። ተንበርክኮም። ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ። ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር። 《የሐ ሥራ 7፥58—60》
🌿❤️ የቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት በረከትና ምልጃው አይለየን ለዘለዓለሙ አሜን
ወስብሓት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን

No comments:

Post a Comment