Pages

Wednesday, September 19, 2018

፹፩ (81) መፅሐፍ ቅዱስ እና ፷፮ (66)

♦በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ! ♦

★መናፍቃኑ ከስልሣ ስድስቱ ውጭ ሌሎች ቅዱሳት መጽሐፍት የለም ወይም አያስፈልግም እንዳይሉ ማስረጃዎችን እነሆ፡-




☞በቀላል አማርኛ 66 ቱ መጽሀፍት ጎደሎ ነው አዲስ ኪዳን ላይ የተጻፍት ክርስቶስ የሚያጣቅስባቸው ነገሮች 66ቱ ውስጥ የሉም 81 ውስጥ ግን በሙሉ አለ ፡፡እንፈልግም ካላችሁ መቁለጭለጭ ነው ትርፉ  ፡፡ለሁሉም ኦርቶዶክስ ጋር ቅረቡ ኢየሱስ ከብሉይ ኪዳን የጠቀሳቸው በሙሉ እኛ እጅ ላይ አለ፡፡እንደመናፍቃን ጉረኛ ባንሆንም ያልተጋነነ ኩራት ይሰማናል፡፡፡

☞መናፍቃኑ ከስልሣ ስድስቱ ውጭ ሌሎች ቅዱሳት መጽሐፍት የለም እንዳይሉ እነሱ አምነው የተቀበሉት 66ቱ መጽሐፍ ቅዱስ እራሱም ይመሰክርባቸው፡፡
☞ማስረጃ 1.
☞ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር ይለናል ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ (ሉቃ.3፡23)
- እንግዲህ ጌታችን አምላካችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከ30 ዓመቱ በፊት የት ነበረ? ምን እየሰራ ነበረ? ብልን ስንጠይቅ መልሱን በ66 መጻሕፍት ውስጥ ሳይሆን በቤተክርስቲያናችን የትውፊት መጻህፍት ውስጥ እድገቱ ምን እንደሚመስል በዝርዝር ተጽፎ እናገኛለን፡፡
☞ማስረጃ 2.

☞በማቴዎስ ወንጌል 27፡3-10 (በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፥ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሌዎች መልሶ፦ ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ። እነርሱ ግን። እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ አሉ። ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ። የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው። የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም አሉ። ተማክረውም የሸክላ ሠሪውን መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት። ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ። በዚያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ የተባለው። ከእስራኤል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን፥ የተገመተውን ዋጋ ሠላሳ ብር ያዙ፥ ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሠሪ መሬት ሰጡት። የሚል ተፈጸመ። በዚያን ጊዜ የነቢዩ የኤርሚያስ ቃል ተፈጸመ ይለናል ይሁዳ…እንዲህ ያለው ‹‹የእስራኤል ልጆች የተስማሙበትን የክቡርን ዋጋ ሠላሳውን ብር ወሰዱ›› ይህን ቃል የምናገኘው በስድሳ ስድስቱ ውስጥ ሳይሆን በተረፈ ኤርሚስ 7፣ 2-4 ባለው ላይ ነው፡፡
- ቅዱስ ማቴዎስ ትንቢተ ኤርሚያስን ጠቅሶ ሲጽፍልን 'በነብዩ ኤርሚያስ የተባለው ብሎን ነው፡፡' ምን ተባለ ስንል ማቴዎስ ''የተባለውን'' ና ''ተፈጸመ'' ያለንን የምናገኘው መናፍቃኑ አንቀበለውም በሚሉት በ81 መጽሐፍት ውስጥ ነው፡፡
እንዲህ ይላል ‹‹እስራኤል ልጆች የተስማሙበትን ዋጋ 30 ብር ይቀበሉታል ያንንም ብር ለሸክላ ሰሪ ቦታ ዋጋ አድርገው ይሰጡታል››
☞ማስረጃ 3.
☞ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26 እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፡፡ ‹‹እንፍጠር›› ሲል ከአንድ በላይ ብዛትን ሲያመለክት 2 ወይም 4 ወይም 10 ሳይሆኑ ስላሴን /ሶስትነት/ ሶስት መሆናቸውን የሚነግረን በሲራክ 2፤22 ሄኖክ 5፤38 ሄኖክ 6፤24 ሄኖክ 13፤14 እዝራ ስቱኤል 4፤56እዝራ ስቱኤል 12፤48 ሲራክ 44፤10 በግልጽ ስላሴ እያለ በማሳየት ነው፡፡ ክብር ለቅድስት ስላሴ ይሁን!
☞ማስረጃ 4.
☞በሉቃስ 14:13-14 ነገር ግን ግብዣ ባደረግህ ጊዜ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንም ዕውሮችንም ጥራ፤
የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤ የሚለውን ኃይለ ቃል ከጦቢት4፣7፡10 የተገኘ ነው ‹‹ከገንዘብህም ምጽዋት ስጥ ምጽዋትም በመጸወትህ ጊዜ በገንዘብህ አትዘን፣ ከድሃም ፊትህን አትመልስ፤ እግዚአብሔርም ገጸ በረከቱን ካንተ አይመልስም፡፡››

✿ቁልፍ ቃል
☞ መፅሀፈ ሄኖክ ፣መፅሀፈ ሲራክ . . .  የእነዚህ እነና የመሳሰሉትን ከሰማንያአሀዱ የተወጣጡ የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅሶች በዚህ ትምህርት ላይ ይገኛሉ እነዚህን ቃላት በስልካችሁ ባለው 81ዱ መፅሀፍ ቅዱስ ብታጡት ምዕራፍ ወይም ጥቅሱ ተሳስቶ ሳይሆን በስልካችሁ ያለው ስለላልተሟላ ነው። ስለሆነም በአቅራቢያችሁ ወደሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤት ቤተመፃህፍት ወይም በቤተክርስቲያን የሚገኙ  ሰማንያ አሀዱ መፅሀፍትን በመጠቀም የምታገኙ መሆኑን በትህትና እገልፃለሁ !
☞ማስረጃ 5.
❀1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4፡2 በጌታ በኢየሱስ የትኛውን ትእዛዝ እንደ ሰጠናችሁ ታውቃላችሁና። ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤ ከዝሙት እንድትርቁ፥ የሚለውን ኃይለ ቃል ከጦቢት4፡12 የተገኘ ነው፡፡
☞ማስረጃ 6.
❀በዮሐንስ ወንጌል 10፡22 በኢየሩሳሌምም የመቅደስ መታደስ በዓል ሆነ፤ … ‹‹የመቅደስ መታደስ በዓል›› በሌሎቹ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አናገኘውም በመጽሐፈ መቃብያን 4 ላይ ብቻ ነው የምናገኘው፡፡
☞ማስረጃ 7.
❀በ ሮሜ 13፡1 ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። የሚለው ኃይለ ቃል ከሲራክ 17፡14 የተወሰደ ነው፡፡
☞ማስረጃ 8.
❀አዳምና ሔዋን አቤልና ቃየልን ወለዱ፡፡ ቃየል ሚስቱን አወቀ ጸነሰችም ይላል ዘፍጥረት 4፡17 በ66ቱ መጽሐፍት ላይ ስለ አቤልና ቃየል መወለድ እንጂ ሌላ የሰው ዘር በምድር ላይ ሰለመኖራቸው ምንም አያወራም፡፡ ታድያ ይህቺ የቃየል ሚስት ከየት መጣች ስለስዋ ምንም አይናገርም በአለም ላይ የነበሩ ሰዎች አራት ብቻ እንደነበሩ ነበር የምናነበው፡፡ የዚህን መልስ የምናገኘው በኩፋሌ 5፡8-17 ላይ ነው፡፡
☞ማስረጃ 9.
❀- ይሁዳ በመልዕክቱ ‹‹የሄኖክን ትንቢት ከመጽሐፈ ሄኖክ ጠቅሶ›› ጽፎታል (ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ። እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል (ይሁዳ 1፡14-15) መጽሐፈ ሄኖክ ደግሞ በስልሣ ስድስቱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም፡፡ እንግዲህ ያልተጻፈውን ከልቡናው አንቅቶ ሄኖክ እንዲህ ብሎ ተናገረ ብሎ ዋሸ አይደለም በእውነት መሠከረ እንጂ፡፡
- ይህን ስለ ጌታችን መድሃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነገረውን ትንቢት ይሁዳ ሲጽፍልን/ሲነግረን ትንቢቱ ምን እንደነበረ፣ ከመጽሐፈ ሔኖክ / 81ዱ መጻሕፍት/ ላይ ነው የሚገኘው፡፡ መጽሐፈ ሄኖክ 1፡9፡፡
☞ማስረጃ 10.
❀1ኛ ቆሮ. 10፡9 ‹‹ከእነርሱም አንዳንዶቹ ጌታን እንደ ተፈታተኑት በእባቦቹም እንደ ጠፉ ጌታን አንፈታተን›› የሚለው ቃል ከዮዲት 8፡24 የተገኘ ቃል ነው፡፡

✿ቁልፍ ቃል
☞ መፅሀፈ ሄኖክ ፣መፅሀፈ ሲራክ፣መፅሀፈ ጥበብ . . .  የእነዚህ እነና የመሳሰሉትን ከሰማንያአሀዱ የተወጣጡ የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅሶች በዚህ ትምህርት ላይ ይገኛሉ እነዚህን ቃላት በስልካችሁ ባለው 81ዱ መፅሀፍ ቅዱስ ብታጡት ምዕራፍ ወይም ጥቅሱ ተሳስቶ ሳይሆን በስልካችሁ ያለው ስለላልተሟላ ነው። ስለሆነም በአቅራቢያችሁ ወደሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤት ቤተመፃህፍት ወይም በቤተክርስቲያን የሚገኙ  ሰማንያ አሀዱ መፅሀፍትን በመጠቀም የምታገኙ መሆኑን በትህትና እገልፃለሁ !
☞ማስረጃ 11.
✿የዮሐንስ ወንጌል 7፡7 ‹‹ዓለም እናንተን ሊጠላ አይቻለውም፤ እኔ ግን ሥራው ክፉ መሆኑን እመሰክርበታለሁና እኔን ይጠላኛል።›› የሚለው የ አምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት በጥበበ 2፡13 ላይ ይገኛል፡፡

☞ማስረጃ 12.
✿ት.ኤር. 39፡16 ስለ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ የተነገረው ትንቢት (ሂድ ለኢትዮጵያዊውም ለአቤሜሌክ እንዲህ በለው። የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ በዚያም ቀን በፊትህ ይፈጸማል። በዚያ ቀን አድንሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም። ፈጽሜ አድንሃለሁ ነፍስህም እንደ ምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ አትወድቅም፥ በእኔ ታምነሃልና፥ ይላል እግዚአብሔር፦) የሚለው ትንቢት ፍጻሜውን የምናውቀው በተረፈ ኤርሚያስ ከምዕ.8 ጀምሮ ስናነብ ነው፡፡

☞ማስረጃ 13
✿1ኛ ቆሮ. 15፡32 ‹‹ሙታንስ የማይነሡ ከሆነ፥ ምን ይጠቅመኛል? ነገ እንሞታለንና እንብላና እንጠጣ።›› የሚለው ቃል ከጥበብ 2፡6 የተገኘ ቃል ነው፡፡ (ኑ ተድላ ደስታ እናድርግ በህጻንነታችን ወራት ሳለን ከዚህ ይህ ቀረን በማለት በሰውነታችን ደስ የሚያሰኘንን ስራ እናድርግ)


☞ማስረጃ 14
✿የሉቃስ ወንጌል 16፡9 ‹‹እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ።›› የሚለው ትምህርት በ መጽሐፈ ሲራክ 14፡13 ላይ ይገኛል፡፡ (ሳትሞት ለባለእንጀራህ በጎ ነገር አድርግ እጅህንም ዘርግተህ የተቻለህን ያህል ስጥ፡፡)
☞ማስረጃ 15
✿በዕለተ ሆሳዕና ዘንባባ ይዘው ጌታችንን የኢየሩሳሌም ሰዎች ሲያመሰግኑት ውለዋል
( ማቴ. 21፡9-15 ‹‹የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም። ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር። ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም። ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው። ማር. 11፡9-10 ‹‹የሚቀድሙትም የሚከተሉትም። ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ በጌታ ስም የምትመጣ የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር። ዮሐ. 12፡13 ‹‹የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡና። ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው እያሉ ጮኹ።)
የዚህ ታሪካዊ ትውፊት አመጣጥ የሚገኘው በዮዲት 15፡12 እና በኩፋሌ 13፡21 ላይ ነው፡፡
☞ማስረጃ 16
✿1ኛ የጴጥ. 1፡24 ‹‹ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤›› የሚለው ቃል ከሲራክ 14፡18 የተገኘ ነው፡፡ (ቅጠሉ ጭፍቅ ያለ የእንጨት ቅጠል የመጀመሪያው ቅጠል እንዲረግፍ ደማዊና ስጋዊ ፍጥረት ሁሉ እንዲሁ ነው ይህ ይወለዳል ያ ይሞታል)
እንግዲህ ከነዚህ ማስረጃዎች የምረዳው ሐዋርያት፣ ነብያት፣ ቀደምት አበው ሁሉ ያስተምሩ የነበሩት ከ46ቱ የብሉያት መጽሐፍ እየጠቀሱ እንደነበር ነው፡፡ ለዚያውስ እነሱ (መናፍቃኑ) የተለያዩ የሞት ፍልስፍና የያዙ መጻሕፍትን እያጻፉ አንብቡ እያሉ ይበትኑስ የለ ታዲያ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሌላ መጽሐፍ አታንብቡ ካሉ እነሱ ለምን ሌላ መጽሐፍ እየጻፉ ያሰራጫሉ ወይስ ትንቢቱ ለኦርቶክሳውያን ብቻ ነው የተነገረው ይሄ ለማጭበርበር ነውና የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸውን መጻሕፍት መርምረን እውነተኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትን የያዙ ከሆነ አንብበን ልንረዳና ልንመራባቸው ተፈቅዶልናል፡፡
እንግዲህ ድርሣናትም ሆኑ ገድላት ስለ እግዚአብሔር አዳኝነት ታላቅነት የሚገልጹ ስለሆነ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው መሆናቸው የተረጋገጠ ነው፡፡ ጳውሎስ ስልሣ ስድስቱን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ተጠቀም አላለም፡፡ ገደብ ሳያደርግ የእግዚአብሔር መንፈስ ያባቸው በቅዱሳን አባቶችም ሆነ በሌሎቹ ክርስቲያኖች የተጻፉትንም መንፈሳዊ መጻሕፍት አለ እንጂ፡፡ በዚህም ምክንያት ሃዋርያዊት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተጨማሪ የብሉይኪዳን መጻሕፍትንና የትውፊት መጻሕፍትን ትቀበላለች ታስተምራለች፡፡

             ~~~ተፈፀመ~~~

☞ይህንን ለመናፍቃን መልስ የሆነ ትምህርት ስንቶቻችሁ ተከታትላችሁታል ?? ትምህርቱስ ጠቅሞአችኋል ?
          ሰብሐት
✥┈┈•◦◈◎❖◎◈◦•┈┈✥
         ✣   ለአብ  ✢
      ✣   ለውልድ   ✣
   ✣   ለመንፈስ ቅዱስ  ✣
✥┈┈•◦◈◎❖◎◈◦•┈┈✥


♥ወስብሃት ለእግዚአብሔር♥           ♥ወለወላዲቱ ድንግል♥     ♥ወለመስቀሉ ክቡር♥
አሜን!!

1 comment: