Pages

Wednesday, September 19, 2018

ከቁርባን በፊት ምን ብለን መፀለይ አለብን?

ከቁርባን በፊት ምን ብለን መፀለይ አለብን?

የቁርባን ፀሎት
✔❤️🙏❤️✔️
ቅዱስ ቁርባን ለምትቀበሉ ሰዎች ወይም ለመቀበል ለተዘጋጃችሁ እህት ወንድሞቼ ልትቆርቡ ስትሉ የምትፀልዩት የተማፅኖ ፀሎት እነሆ። ✔️
✠☞✞✞ ቅዱስ ቁርባን ለሚቀበሉ እንዲህ ይበሉ (ይፀልዩ) ✞✞☜✠


❤️❤️❤️የሁሉን ልብ የምታውቅ በቅዱሳን መካከል የምትኖር ቅዱስ አምላክ ሆይ ሀጢያት የሌለብህ አንተ ብቻ ነህ ሀጢአት የምታስተሰርይ ይቅርባይም አንተ ነህ።
❤️❤️❤️አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ ደስ የሚያሰኝህ መስዋእት የልጅህ ስጋ እነሆ በዚህም ሀጢአቴን ሁሉ አቅልልኝ ስለ እኔ አንድ ልጅህ ሞቷልና ስለ እኔ በቀራኒዮ የፈሰሰ ንፁህ የሚሆን የመሲህም ደም እነሆ ስለ እኔ ይጮሀል ይህ የሚናገር ደም የእኔን የባርያህን ሀጢአት የሚያስተሰርይ ይሁን ስለ እነርሱም ልመናዬን ተቀበል ወዳጅህ ስለ እኔ ጦርንና ቅንዋትን ተቀብሏልና ደስ ያሰኝህም ዘንድ ታመመ ከዳንኩም በኋላ ሰይጣን ወደ ልቦናዬ ተመልሶ በፍላፆቹ ወጋኝ አቤቱ ምህረትህን ስጠኝ ፅኑ ከሳሽ ነውና ሀጢአትንም ምክንያት አድርጎ ገደለኝ እኔን ከህይወቴ ማሳትን በቃኝ ከማይል ደፋር አድነኝ አቤቱ ንጉሴና አምላኬ መድሀኒቴም የምትሆን አንተ የእኔን የባርያህን የነፍሴንና የስጋዬን ቁስል አድርቅልኝ።
❤️❤️❤️ጌታ ሆይ ለዚህ የተቀደሰ ምስጢር አለመግባቴን አውቃለሁ በክብርህ ፊት ልቀርብና አፌን እከፍት ዘንድ አልደፍርም ነገር ግን በይቅርታህ ብዛት ፀጋህን ሰጥተህ ለክብርህ የተገባሁ አድርገኝ መተላለፌን ሁሉ ይቅር በለኝ።
❤️❤️❤️ "አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ርኵስት ከሆነች ከቤቴ ጠፈር በታች ትገባ ዘንድ የሚገባኝ አይደለም።እኔ አሳዝኜሃለሁና በፊትህም ፉክ ሥራ ሠርቻለሁና በአርኣያህና በአምሳልህ የፈጠረኸዉ ሥጋዬንና ነፍሴን ትእዛዝህን በማፍረስ አሳድፌአለሁና ሥራም ምንም የለኝምና።ነገር ስለ መፍጠርህና እኔን ለማዳን ሰዉ ስለ መሆንህ ስለ ክቡር መስቀልህም ማሕየዊት ሰለ ምትሆን ስለ ሞትህ በሦስተኛው ቀን ስለ መነሣትህም ጌታዬ ሆይ ከበደልና ከመርገም ሁሉ ከኃጢአትና ከርኵሰትም ሁሉ ታነጻኝ ዘንድ እለምንሃለሁ እማልድሃለሁም።
❤️❤️❤️የቅድስናህንም ምስጢር በተቀበልሁትጊዜ ለወቀሳ ለመፋራረጃ አይሁንብኝ ማረኝ ይቅርም በለኝ እንጂ። የዓለም ሕይወት ሆይ በርሱ የኃጢአቴን ሥርየት የነፍሴንም ሕይወት ስጠኝ እንጂ።
❤️❤️❤️በሁለት ወገን ድንግል በምትሆን በወለደችህ በእመቤታችን በቅድስት ማርያም በመጥምቁ ዮሀንስም አማላጅነት በቅዱስ ሚካኤል በቅዱስ ገብርኤል ጥበቃና ተራዳኢነት ክቡራን በሚሆኑ በመላእክትም በሰማእታትም ሁሉ ፀሎት እስከ ዘለአለሙ ድረስ አሜን።"
{ ቅዳሴ ሐዋርያት}
❤️❤️❤️
✥ ✥ ✥

No comments:

Post a Comment