Pages

Wednesday, September 19, 2018

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን 


#አንድ_ጌታ
#አንድ_ሀይማኖት
#አንድ_ጥምቀት ። (ኤፌ 4፥5)
መጽሐፍትን ማስተዋልና መመርመር ያስፈልጋል ።
✍ ጥንት አባቶቻችን በዘመናቸው መናፍቃን ካህናት፣አላውያን መኳንት ፣ ከሀዲያን ነገስታት ሲነሱባቸው ብራና ደምጠው ፣ ቀለም በጥብጠው ፣ ብዕር ቀርፀው ፣ ተግሳስ ጽፈው በቂ ምላሾችን ሲሰጡ ቆይተዋል። አርዮስ ሲነሳ ፤ አትናቲዮስ ፣ ንስጥሮስ ሲነሳ ፤ ቄርሎስ በቂና ከበቂ በላይ የሆኑ መልሷቻቸውን መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት አድርገው ሰተዋል። ዛሬላይ በዘመናችን እየተነሱ ያሉ ጥያቄዎች እንዲሁም ዕለት ዕለት እየተስፋፋ የመጣውን የምንፍቅናን ትምህርት ጥንት አባቶቻችን በዘመናቸው ሲያደርጉት እንደነበረው



መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት በማድረግ << የእግዚአብሔር ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ ፥ የኑሮአቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው ።(ዕብ13 ፥7)>> ተብሎ እንደተጻፈው እኛም የቀድዎቹን የእምነት አባቶቻችንን በመምሰል ዛሬ ላይ ከመካከላቸው አንድኳን የሚያስተውል ቢኖር ወደ እውነት እንዲመለሱ ከአባቶቻችን የተሰጠንን ትምህርት እንነግራቸዋለን ።
��የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ከግሪክ እና ከሮም የቀደመ የመጀመሪያው ኦርቶዶክስ እምነት ነው ።
( በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 )
(በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 8)
(በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 10) ላይ የምናገኘው። ገና ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ እንዳደረባቸው ፤ መንፈስ ቅዱስም ባደረባቸውም ሰዓት (ምዕራፍ 2) ላይ ኢትዮጵያውያንም እዛው ነበሩ ።
(በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 8 ፥ 39-38) ላይ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ እየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምኖ በፊልጶስ እጅ ሲጠመቅ ፤ ተጠምቆም ወንጌልን ይሰብክ ነበር ሮማዊው #ቆርኔልዎስ ግን ( በሐዋርያት ሥራ 10) ገና ነበር ።
በ313 church history (የቤተክርስቲያን ታሪክ) እንደምናውቀው በወቅቱ በነበሩት አላውያን መኳንትና ነገስታት በዝተው በነበሩት ሰዓት ቤተክርስቲያን አይሰራም ነበር ፤ ወንጌልን መስበክ አይቻልም ተብሎ በነበረበት ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ በነበሩት አባቶች ለእምነታቸው እና ለሀይማኖታቸው እንደ ሻማ ቀልጠው እንደ ጧፍ አብርተው ወንጌ አስፋፍተው ነበር ። #አስተውሉ_ኦርቶዶክስ_ለክርስትና_መነሻ_የእምነት_እና_የሐይማኖት_መጀመሪያ_ናት ።
✅በተጨማሪም ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ አይደለም በማለት የተለያዩ የምንፍቅና ትምህርታቸውን በተሳሳተ መንገድን ሲያስተምሩና ጥያቄንዎችን ሲያነሱ የምናያቸው ሙስሊም ወንድምና እህቶቻችንን። እግዚአብሔር በፈቀደና በወደደ መጠን እነሱ በሚረዱበት በራሳቸው የመጽሐፍ አጻጻፍ በመከተል መጽሐፍትን በመመርመርና በማጤን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልስ እንደሚከተለው እናቀርባለን ።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነቱን ክደው አምላክ አይደለም በማለት የተሳሳተ የምንፍቅና ትምህርታቸውን እያስተማሩ ይገኛሉ። ይህ ትምህርታቸው በሌላ መልኩ ኣላህ አምላክ አይደለም እያላችሁ ነው። ሂሳቡን አብረን እናስላው።
✅በእስልምና ትምህርት አላህ 99 ስሞች እንዳለው ይነገራል። እነዚህ 99 ስሞችን የማያምን ሁሉ ከሐዲ ይባላል። ከነዚህ 99 የአላህ ስሞች መካከል ለጊዜው ስድስቱን (6)እንመለከታለን። ታድያ ይህንን ስንናገር መፅሐፍ ቅዱስ ቁራንን በ600 ዓመት እንደሚበልጠውና ቁራን ከመፅሐፍ ቅዱስ የተኮረጀ መሆኑንም ግንዛቤ ውስጥ እናስገባ።
👉 (1) አል-ሓቅ ( the truth) የሚል ነው። አላህ ስሙ አል ሐቅ ወይም በአማርኛ እውነት ማለት ከሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ እውነት ነኝ አላለም ወይ??? ብሏል። ዮሀ 14:6 እኔ እውነት ነኝ ታዲያ ለምን አላህን ትክዳላችሁ???
👉(2) አል-ባዐት (resurrection) በአማርኛ ትንሳኤ የሚል ነው። ታዲያ ኢየሱስ እኔ ትንሳኤ ነኝ አላለም??? ብሏል። ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ። ዮሀ 11:25-26
👉(3) አል-አዋል ወአል-አዀር ( the beginning and the end) በግሪክኛ አልፋና ኦሜጋ በአማርኛ የመጀመሪያውና የመጨረሻው የሚል ነው። ታዲያ ኢየሱስ እኔ አልፋና ኦሜጋ ወይም የመጀመሪያና የመጨረሻ ነኝ አላለም???? ብሏል። ራእ 1:7-8 22:13 አልፋና ኦሜጋ ፊተኛውና ኋለኛው መጀመርያው እና መጨረሻው እኔ ነኝ
👉(4) አል-ማሊክ ( king of kings) ወይም በአማርኛ የነገሥታት ንጉሥ የሚል ነው። ታዲያ ኢየሱስ የነገሥታት ንጉሥ አይደለም??? ነው። ራእ 17:14 በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለሆነ....
👉(5) አል-ሀዲ ( guide) በአማርኛ መግቢያ በር ወይም መሪ የሚል ነው።ታዲያ ኢየሱስ በሩ እኔ ነኝ አላለም??? ብሏል። ዮሐ 10:9 >
👉(6) አል-ኑር ( the light) በአማርኛ ብርሃን የሚል ነው። ታዲያ ኢየሱስ እኔ ብርሃን ነኝ አላለም???? ብሏል። ዮሀ 8:12 እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ ማን ነው ከሐዲ? ክርስቲያኖች ወይስ እስላሞች?
ሙስሊሞች በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ካላችሁበት ጨለማ ተላቅቃችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትመለሱ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። በማታምኑበት እምነት የዘመድ የጓደኛ ይሉኝታ ይዟችሁ ከአምላካችሁ እርቃችሁ እስከመቼ? ውጡ ከዚህ ድቅድቅ ጨለማ! ክብር ሁሉ ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለፈጣሪያችን ለድንግል ማርያም ልጅ ለወረደው ለተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን። አሜን!
#አንድ_ጌታ
#አንድ_ሀይማኖት
#አንድ_ጥምቀት።(ኤፌ 4፥5)
የተወደዳችሁ እህትና ወንድሞች ሆይ ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት የሲኦል ደጆች አይችሏትም ቤተክርስቲያን አትታደስም! የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን ።
ወስበሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

No comments:

Post a Comment